ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።
ሕዝቅኤል 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ ግንቡ በሚፈርስበት ጊዜ፦ የቀባችሁት ኖራ የት አለ? አይሉአችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ ካቡ ሲፈርስ ሕዝቡ “የለሰናችሁበት ኖራው ወዴት ሄደ?” ብለው አይጠይቋችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግድግዳው በሚፈርስበት ጊዜ የቀባችሁት ቀለም የት አለ ብለው ሰዎች አይጠይቁአችሁምን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ ግንቡ በወደቀ ጊዜ፦ የመረጋችሁት ምርግ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ፦ የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን? |
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።
ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም እዚያ ውስጥ አስገባችው፥ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።
ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።
ከዚያም ዜቡል፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜልክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልካቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።