Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነሆ ግንቡ በወ​ደቀ ጊዜ፦ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁት ምርግ ወዴት አለ? አይ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነሆ ካቡ ሲፈርስ ሕዝቡ “የለሰናችሁበት ኖራው ወዴት ሄደ?” ብለው አይጠይቋችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነሆ ግንቡ በሚፈርስበት ጊዜ፦ የቀባችሁት ኖራ የት አለ? አይሉአችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ግድግዳው በሚፈርስበት ጊዜ የቀባችሁት ቀለም የት አለ ብለው ሰዎች አይጠይቁአችሁምን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ፦ የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 13:12
11 Referencias Cruzadas  

ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው።


ደግ​ሞም ሊሸ​ሽ​ጉት በአ​ል​ቻሉ ጊዜ እናቱ የደ​ን​ገል ሣጥን ለእ​ርሱ ወስዳ ዝፍ​ትና ቅጥ​ራን ለቀ​ለ​ቀ​ችው፤ ሕፃ​ኑ​ንም አኖ​ረ​ች​በት፤ በወ​ን​ዝም ዳር ባለ በቄ​ጠማ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጠ​ችው።


ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?


ያለ ገለ​ባም ለሚ​መ​ር​ጉት ሰዎች፦ ይወ​ድ​ቃል በላ​ቸው። የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ ይዘ​ን​ባል፤ ታላ​ቅም የበ​ረዶ ድን​ጋይ በራ​ሳ​ቸው ላይ አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ለኛ ዐውሎ ነፋ​ስም ይሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋል።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ ትታ​መ​ኑ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩት አማ​ል​ክት የት አሉ?


ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።”


ዜቡ​ልም፥ “እን​ገ​ዛ​ለት ዘንድ አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? ያል​ህ​በት አፍህ አሁን የት አለ? ይህ የና​ቅ​ኸው ሕዝብ አይ​ደ​ለ​ምን? አሁ​ንም ወጥ​ተህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተዋጋ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos