ዘፀአት 36:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው መጋረጃ አደረገ፥ አምሳ ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ መጋጠሚያ አደረገ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንደኛው መጋረጃ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው ተጋጥሞ ከተሰፋው በስተመጨረሻ ካለው መጋረጃ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን እርስ በርሳቸው ትይዩ በማድረግ ሠሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያ መጋረጃ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል መጨረሻ መጋረጃ ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት የሚሆኑ ኀምሳ ቀለበቶች አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ። |
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞም ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አድርግ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት እንዲሆኑ አድርግ።
በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ በመጋጠሚያው ላይ የሰማያዊው ግምጃ ቀለበቶች አደረገ፤ ደግሞ በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በመጋጠሚያው ላይ እንዲሁ አደረገ።