ዘፀአት 29:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነሱ እጃቸው ሙሉ እንዲሆንና የተቀደሱ እንዲሆኑ ማስተስረያ የሆነውን ነገር ይብሉት፤ የተቀደሰ ስለሆነ ሌላ ሰው አይብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክህነታቸውና ለመቀደሳቸው ማስተስረያ የሆኑትን እነዚህን መሥዋዕቶች ይብሉ፤ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ሌላ ማንም አይብላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነት ሥልጣን ሲቀበሉ ስለ ኃጢአት ይቅርታ የተሠዋውንም ይብሉ። ይህ ምግብ የተቀደሰ ስለ ሆነ ካህናት ብቻ ይብሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመክበራቸው እጆቻቸውን ይቀድሱ ዘንድ በተቀደሱበት በዚያ ቦታ ይብሉት፤ የባዕድ ልጅ ግን አይብላው፤ የተቀደሰ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተካኑና የተቀደሱ ይሆኑ ዘንድ ማስተስረያ የሆነውን ነገር ይብሉት፤ ሌላ ሰው ግን አይብላው፤ የተቀደሰ ነውና። |
ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እጅግ የተቀደሰ ነውና ለጌታ ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የተረፈውን የእህሉን ቁርባን ውሰዱ፥ እርሾም ያልገባበት ቂጣ አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤
በቆሬና በእርሱም ተከታዮች ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በጌታ ፊት ዕጣንን ለማጠን እንዳይቀርብ፥ ጌታ በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።
ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ግዴታዎች ይፈጽሙ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
በማደሪያውም ፊት በምሥራቅ በኩል በመገናኛው ድንኳን ፊት በስተ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ በመቅደሱም ውስጥ ማናቸውንም ለእስራኤል ልጆች የሚደረገውን ሥርዓት ይጠብቃሉ፤ ማናቸውም ልዩ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።