በምሰሶዎቹም ራስ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ያስጌጡ ዘንድ በሰባት ረድፍ የተሠሩ መረቦችን ሠራ፤ አንዱን መረብ ለአንድ ጉልላት፥ ሁለተኛውን መረብ ለሁለተኛው ጉልላት አደረገ።
ዘፀአት 28:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎችን በደረቱ ኪስ ጫፎች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች ታስገባቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን የወርቅ ጕንጕኖች በደረት ኪሱ ጐኖች ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋራ አያይዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች ከሁለቱ ቀለበቶች ጋር አያይዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተጐነጐኑትንም ሁለቱን የወርቅ ቋዶች በልብሰ እንግድዓው በሁለት ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለት ቀለበቶች ታገባቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተጎነጎኑትንም ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች ታገባቸዋለህ። |
በምሰሶዎቹም ራስ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ያስጌጡ ዘንድ በሰባት ረድፍ የተሠሩ መረቦችን ሠራ፤ አንዱን መረብ ለአንድ ጉልላት፥ ሁለተኛውን መረብ ለሁለተኛው ጉልላት አደረገ።