ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ንድፈ ሐሳቡን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ዘፀአት 27:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሳንቃዎች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ይሥሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያውን ውስጡን ባዶ ከሆኑ ሳንቃዎች አብጀው፤ ልክ በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ይበጅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሠዊያውን ከሳንቃዎች ሥራ፤ ውስጡም ባዶ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሌዳውም ፍልፍል ይሁን፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳንቆች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ያድርጉት። |
ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ንድፈ ሐሳቡን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ።