ሙሴም፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእርሱ አንድ ዖሜር ሙሉ በትውልዳችሁ ሁሉ ይጠበቅ” አለ።
ዘፀአት 16:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንን አለው፦ “አንድ ማድጋ ወስደህ ዖሜር ሙሉ መና አኑርበት፥ በትውልዳችሁም ተጠበቆ እንዲኖር በጌታ ፊት አስቀምጠው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ወስደህ አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለሚመጡት ትውልዶች እንዲቈይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም አሮንን “አንድ የሸክላ ዕቃ ወስደህ አንድ ኪሎ ተኩል በሚይዝ መስፈሪያ መና አኑርበት፤ ለመጪውም ትውልድ በእግዚአብሔር ፊት ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንን፥ “አንድ የወርቅ መሶብ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፤ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እሮንን፦ አንድ ማድጋ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፥ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው አለው። |
ሙሴም፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእርሱ አንድ ዖሜር ሙሉ በትውልዳችሁ ሁሉ ይጠበቅ” አለ።
በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል።