ዘዳግም 26:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ በጌታ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑም ቅርጫቱን ተቀብሎ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ዕንቅቡን ከእጅህ ወስዶ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ያኑረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዕንቅቡን ከእጅህ ወስዶ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠውያ ፊት ያኑረው። |
በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፥ ‘ጌታ ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደገባሁ ዛሬ በጌታ እግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ’ በለው።
አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።