ቈላስይስ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማመስገን ጋር በጸሎት ውስጥ ነቅታችሁ ያለማቋረጥ ትጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማመስገን ጋራ ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን ተግታችሁ በማመስገን ባለማቋረጥ ጸልዩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምስጋና እየተጋችሁ ለጸሎት ፅሙዳን ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤ |
ስለዚህ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የፈቃዱን እውቀት እንድትሞሉ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።
ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት ጌታን እንዳልበድል ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።