ሐዋርያት ሥራ 23:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ “ይህን ብላቴና ወደ ሻለቃው ውሰድ፤ የሚያወራለት ነገር አለውና፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም ከመቶ አለቆቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ይህ ልጅ ለጦር አዛዡ የሚነግረው ነገር ስላለ ወደ እርሱ ውሰደው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ “ይህ ልጅ ለጦር አዛዡ የሚናገረው ነገር ስላለው ወደ እርሱ አቅርበው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ፥ “የሚነግረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻለቃው አድርስልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ፦ ይህን ብላቴና ወደ ሻለቃው ውሰድ፥ የሚያወራለት ነገር አለውና አለው። |
እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና “ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ፤” አለው።
ከመቶ አለቆቹም ሁለት ጠርቶ “ወደ ቂሣርያ ይሄዱ ዘንድ ሁለት መቶ ወታደሮችንና ሰባ ፈረሰኞችን ሁለት መቶም ባለ ጦር መሣሪያዎችን ከሌሊቱ በሦስተኛው ሰዓት አዘጋጁ፤” አላቸው።