ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና “ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞቹ ንገሩ፤” አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 12:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋም ጊዜ “ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን?” ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ወታደሮቹ፣ “ጴጥሮስ የት ገባ?” እያሉ በመካከላቸው ትልቅ ትርምስ ተፈጠረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነጋም ጊዜ ወታደሮቹ “ጴጥሮስ ምን ደርሶበት ይሆን?” በማለት እጅግ ታወኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋ ጊዜም ወታደሮች፥ “ጴጥሮስ ምን ሆነ?” ብለው ታወኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋም ጊዜ፦ “ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን?” ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ። |
ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና “ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞቹ ንገሩ፤” አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።