ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።
2 ነገሥት 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንዕማን ከጭፍሮቹ ሁሉ ጋራ ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ ሄደ፤ በፊቱም ቆሞ፣ “እነሆ በእስራኤል አገር እንጂ በዓለም ሁሉ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ተረድቻለሁ፤ ስለዚህ አሁንም ከአገልጋይህ ስጦታ እንድትቀበል እለምንሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ፤ አሁንም ከባሪያህ ገጸ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ። |
ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።
ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ጌታ ሆይ! አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንክን፥ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔን፥ እኔም ይህን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፤
እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።
አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁም? ወይስ አላሳየኋችሁም? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ አንድም አላውቅም።
እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ።
መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል።
ሳኦልም አገልጋዩን፥ “ብንሄድስ ለሰውየው ምን እንሰጠዋለን? በስልቻዎቻችን የያዝነው ስንቅ አልቋአል፤ ለዚያ የእግዚአብሔር ሰው የምንሰጠው ስጦታ የለንም፤ ምን አለን?” አለው።