La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 25:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መላው የሰራዊቱ ጦር አለቆችና ሰዎቻቸው የባቢሎን ንጉሥ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ጎዶልያስን መሾሙን ሲሰሙ፣ እርሱ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፤ እነርሱም የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ የነጦፋዊው የተንሑሜት ልጅ ሠራያ የማዕካታዊው ልጅ ያእዛንያና ሰዎቻቸው ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች ሁሉ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ሬ​ያን ልጅ ዮሐ​ናን፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የተ​ን​ሑ​ሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማ​ዕ​ካ​ታ​ዊው ልጅ አዛ​ንያ፥ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ጎዶ​ል​ያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶ​ልያ ወደ መሴፋ መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጭፍሮቹም አለቆች ሁሉ፥ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ ሠራያ፥ የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ፥ ሰዎቻቸውም የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያስን እንደ ሾመ በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 25:23
6 Referencias Cruzadas  

አሆሃዊው ጻልሞን፥ ነጦፋዊው ማህራይ፥


ገዳልያም እነርሱንና ወታደሮቻቸውን እንዲህ አላቸው፤ “ከባቢሎናውያን ባለ ሥልጣኖች የተነሣ ምንም ዓይነት ፍርሀት ሊያድርባችሁ እንደማይገባ ቃል እገባላችኋለሁ፤ በዚህች ምድር ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁሉ ነገር ይቃናላችኋል።”


እርሱም ገና ሳይመለስ፦ የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፥ ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ፤ ወይም ለመሄድ ትክክል መስሎ ወደሚታይህ ስፍራ ሁሉ ሂድ።” የዘበኞቹም አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶት አሰናበተው።


ምጽጳ፥ ከፊራ፥ ሞጻ፥