2 ቆሮንቶስ 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ በእናንተ መካከል የጀመረውን ይህንን የቸርነት ከፍጻሜ እንዲያደርሰው ለምነነው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ቲቶ፣ በእናንተ መካከል ቀደም ሲል የጀመረውን የልግስና ሥራ ከፍጻሜ እንዲያደርስ ለምነነው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሥራ አስቀድሞ የጀመረው ቲቶ ስለ ነበረ አሁንም ይህንኑ የልግሥና ሥራችሁን ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ እርሱኑ ለምነነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም የቸርነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈጽምላችሁ ዘንድ ቲቶን ማለድነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ እንደ ጀመረ እንዲሁ ደግሞ ይህን ቸር ሥራ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ሊፈጽም ለመንን። |
ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን?
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።
ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፥ እናንተን ለማገልገል አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖር፥ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።
እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ።
ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል።