ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን?
2 ቆሮንቶስ 8:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ምክራችንን ብቻ አይደለም የተቀበለው፥ ከቀድሞው የበለጠ በመትጋት፥ ወዶ ወደ እናንተ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ቲቶ ወደ እናንተ የመጣው ልመናችንን በመቀበል ብቻ ሳይሆን፣ በታላቅ ጕጕትና በራሱ ፈቃድ በመነሣሣት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲቶ ወደ እናንተ የሚመጣው በራሱ ፈቃድ ተነሣሥቶ በደስታ ነው እንጂ እኛ ስለ ለመንነው ብቻ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልመናችንንም ተቀብሎ፥ ጨክኖ ወደ እናንተ ይመጣ ዘንድ ቸኵሏል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምክራችንን ተቀብሎአልና፥ ትጋት ግን ስለ በዛበት ወዶ ወደ እናንተ ይወጣል። |
ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን?