በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡት፥ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ፥ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ’ በሉ።
2 ዜና መዋዕል 6:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አምላክ ሆይ! የቀባኸውን ሰው አታሳፍረው ለባርያም ለዳዊት ያደረግህለትን ጽኑ ፍቅር አስብ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ የቀባኸውን ሰው አትተወው፤ ለባሪያህ ለዳዊት ቃል የገባህለትን ጽኑ ፍቅር ዐስብ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ የቀባኸውን ንጉሥ አትተወው፤ ለአገልጋይህ ለዳዊት ያደረግህለትን ፍቅር አስታውስ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ከቀባኸው ሰው ፊትህን አትመልስ፤ ለባሪያህም ለዳዊት ምሕረትን አስብ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ አምላክ ሆይ! የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ ለባሪያም ለዳዊት ያደረግህለትን ምሕረት አስብ።” |
በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡት፥ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ፥ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ’ በሉ።
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።