1 ጢሞቴዎስ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ያለማቋረጥ በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራስን ከመግዛት ጋር ብትኖር፥ ሴት ልጅ በመውለድ ትድናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ሴት በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሴት በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ብትጽናና ራስን በመቈጣጠር ብትኖር ልጅ በመውለድ ትድናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። |
ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል።
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን።
ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን ራሳችንን በመቈጣጠርና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ይመክረናል፤