ከዚያም ዳዊት፥ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።
1 ሳሙኤል 25:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ግን የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፥ ለጋሊም ተወላጅ ለሌሳ ልጅ ለፓልጢ ሰጥቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ግን የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፣ ለጋሊም ተወላጅ ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ በዚህ እንዳለ ሳኦል የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን የጋሊም ተወላጅ ለሆነው ለላዊሽ ልጅ ለፓልጢ ዳረለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦል ግን የዳዊትን ሚስት ልጁን ሜልኮልን ሀገሩ ሮማ ለነበረው ለያሚስ ልጅ ለፈልጢ ሰጣት። |
ከዚያም ዳዊት፥ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።
ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎቹ ሄደው ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ ለንጉሡ ዐማች ይሆን ዘንድ፥ ሸለፈታቸውን አምጥቶ በቁጥራቸው ልክ ለንጉሡ አቀረበ፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ዳረለት።