ሺምዒም “ንጉሥ ሆይ! ውሳኔህ ትክክል ነው፤ እኔ አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ” ሲል መለሰ፤ ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።
1 ነገሥት 20:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አክዓብም “ለጌታዬ ለንጉሥ ቤንሀዳድ አንተ ባልከው እስማማለሁ፤ እኔና የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው።” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ልክ እንዳልኸው ነው፤ እኔም ሆንሁ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አክዓብም “ለጌታዬ ለንጉሥ ቤንሀዳድ አንተ ባልከው እስማማለሁ፤ እኔና የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው።” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክዓብም አዝኖ ሄደ፤ በአልጋውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸፋፈነ፤ እንጀራንም አልበላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢይዝራኤላዊውም ናቡቴ “የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም፤” ብሎ ስለ ተናገረው አክዓብ ተቆጥቶና ተናድዶ ወደ ቤቱ ገባ። በአልጋውም ላይ ተጋድሞ ፊቱን ተሸፋፈነ፤ እንጀራም አልበላም። |
ሺምዒም “ንጉሥ ሆይ! ውሳኔህ ትክክል ነው፤ እኔ አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ” ሲል መለሰ፤ ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።
ከጥቂት ጊዜም በኋላ እነዚያው መልእክተኞች ከንጉሥ ቤንሀዳድ ሌላ ትእዛዝ ይዘው እንደገና ወደ አክዓብ መጡ፤ ትእዛዙም እንዲህ የሚል ነበር፤ “ብርህንና ወርቅህን፥ ሚስቶችህንና ልጆችህን እንድታስረክበኝ መልእክት ልኬብህ እንደ ነበር ይታወሳል።
ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።