አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆነ፥ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ከአንተው ጋር ይሁን’ ትላለች።”
1 ነገሥት 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጉምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ መለሰላት፤ ከንጉሡ የተሰወረና ሊመልስላት ያልቻለው አንድም ጥያቄ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጒምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዐይነት እንቆቅልሽ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ያልተረጐመላትና ከንጉሡ የተሰወረ ነገር አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ሊፈታላት ያልቻለውና ከንጉሡ የተሰወረ ነገር አልነበረም። |
አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆነ፥ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ከአንተው ጋር ይሁን’ ትላለች።”
አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም የነገሩን መልክ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ ያለው ጥበብ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ ስለሚመስል፥ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫኑ ሽቶ፥ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በሐሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት።
እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የበለጠ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ።
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።