La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባርያ ሆነህ ተጠርተህ እንደሆነ አይገድህም፤ ነጻ ልትወጣ ቢቻልህ ግን ነጻነትን ተቀበል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በተጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርህን? በዚህ አትጨነቅ፤ ነጻነትህን ማግኘት ከቻልህ ግን ነጻነትህን ተቀበል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርክን? ብትሆንም ግድ የለም፤ አትጨነቅበት፤ ነጻ የመውጣት ዕድል ብታገኝ ግን ይህ ዕድል አያምልጥህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ ባርያ ሳለህ ብታ​ምን አያ​ሳ​ዝ​ንህ፤ የሚ​ቻ​ልህ ከሆነ ግን ነጻ​ነ​ት​ህን አግኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:21
14 Referencias Cruzadas  

እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፤ አታወላውሉም፤


“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤


አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።


እያንዳንዱ ሲጠራ በነበረበት ሁኔታ ይኑር።


ባርያ ሆኖ ሳላ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ የክርስቶስ ባርያ ነው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ የለም፥ ባርያ ወይም ነጻ ሰው የለም፥ ወንድ ወይም ሴት የለም።


ይህን ስል ስለሚያስፈልገኝ ነገር እያማረርሁ አይደለም፤ ያለኝ ነገር ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።


በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በምንም ዓይነት ነገር አትጨነቁ።


በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።


ሕይወታችሁ ከፍቅረ ንዋይ የጸዳ ይሁን፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ “አልለቅህም፤ ከቶም አልተውህም፤” ብሎአልና ያላችሁ ይብቃችሁ።


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።