ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
1 ቆሮንቶስ 14:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልሳን የሚናገር ቢኖር፥ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት በየተራ ይናገሩ፤ አንዱ ደግሞ ይተርጉም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልሳን የሚናገር ቢኖር፣ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት በየተራ ይናገሩ፤ ሌላው ደግሞ ይተርጕም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ቢኖሩ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በየተራ ይናገሩ፤ እነርሱ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጒም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቋንቋ የሚናገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየሆኑ በተራ ይናገሩ፤ ሌላውም ይተርጕምለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤ |
ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።
ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፥ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።