Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 14:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ቢኖሩ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በየተራ ይናገሩ፤ እነርሱ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጒም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በልሳን የሚናገር ቢኖር፣ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት በየተራ ይናገሩ፤ ሌላው ደግሞ ይተርጕም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በልሳን የሚናገር ቢኖር፥ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት በየተራ ይናገሩ፤ አንዱ ደግሞ ይተርጉም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየ​ሆኑ በተራ ይና​ገሩ፤ ሌላ​ውም ይተ​ር​ጕ​ም​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 14:27
6 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ለአንዱ ተአምራትን የማድረግ ኀይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው የትንቢትን ቃል የመናገር ችሎታ ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ ስጦታዎች ከመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ወይም ከርኩሳን መናፍስት መሆናቸውን ለይቶ የማወቅ ችሎታን ይሰጠዋል፤ እንዲሁም ለአንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታን ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የመተርጐም ችሎታን ይሰጠዋል፤


ስለዚህ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው የመተርጐም ችሎታ እንዲኖረው ይጸልይ።


በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ ምሥጢር የሆነውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ስለሚናገር የሚናገረውን ቃል የሚያውቀው የለም።


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።


የሚተረጒም ሰው ከሌለ ግን በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩት በስብሰባ ላይ ዝም ይበሉ፤ ለራሳቸውና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገሩ።


ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos