1 ዜና መዋዕል 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየትውልዳቸው መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ሀያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺሕ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተወላጆቻቸው ቤተሰቦች ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ኻያ ሺህ ሁለት መቶ ወንዶች መሆናቸው መዝገቡ ያስረዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየትውልዳቸውም መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየትውልዳቸው መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን፥ ኀያላን ሰዎች ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። |
የቤኬርም ልጆች፤ ዝሚራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ አብያ፥ ዓናቶት፥ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።