ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’” አለው።
1 ዜና መዋዕል 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይዲኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች፤ የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን። የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳአር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይዲዕኤል፥ ቢልሃን ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ቢልሃም ያዑሽ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ከናዕና፥ ዜታን፥ ታርሺሽና አሒሻሐር ተብለው የሚጠሩ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይዴኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኬሳአር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይዲኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ። |
ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’” አለው።
እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ውግያ የሚወጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።