1 ዜና መዋዕል 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፦ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ማን ይሰጠኛል?” ብሎ ተመኘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣ “ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጕድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “በቤተልሔም ቅጽር በር አጠገብ ካለው የውሃ ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን በሰጠኝ!” ብሎ ተመኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ይሰጠኛል?” ብሎ ተመኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ምንጭ ውሃ ማን ይሰጠኛል?” ብሎ ተመኘ። |
እነዚህም ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት በመካከላቸው ጥሰው አለፉ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልፈለገም፥ ነገር ግን ለጌታ እንደ መባ አፈሰሰው፤
ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።