1 ዜና መዋዕል 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ይባል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ በእርሱ ዘመን የዓለም ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ የመጀመሪያው ልጅ ፌሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ሁለተኛው ደግሞ ዮቅጣን ተብሎ ተጠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኤቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፋፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ። |