ባሉበት ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
ንጉሥ ጠረክሲስም ለንግሥት አስቴርና ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እነሆ ሐማ አይሁድን ለማጥፋት ስላቀደ፣ ቤት ንብረቱን ለአስቴር ሰጥቻለሁ፤ እርሱንም በዕንጨት ላይ ሰቅለውታል።
ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤ ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።
እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው። ሴላ
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ
እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤ አምላክ በማለዳ ይረዳታል።
የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።
“እኔ እንደዚህ እናገራለሁ” ብልማ ኖሮ፣ የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር።
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።
የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነውና።
“እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” ማለት ነው።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።
በሰፈር በዕርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተንቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።