እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ
ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ? እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ
እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ ጌታ ግን ያስብልኛል። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬም ነህና፤ አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ።
ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣ በነገር ጠዘጠዙኝ፣ ዐጥንቴም ደቀቀ።
አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው።
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።
“ ‘እኔ እግዚአብሔር በዚያ እያለሁ፣ “እነዚህ ሁለት ሕዝቦችና ሁለት አገሮች የእኛ ይሆናሉ፤ እኛም እንወርሳቸዋለን።” ብለሃልና፤
አሁንም ቢሆን የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዋሽንቱን፣ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ፣ እኔ ላቆምሁት የወርቅ ምስል ተደፍታችሁ ለመስገድ ዝግጁ ከሆናችሁ መልካም! ባትሰግዱለት ግን ወዲያውኑ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ታዲያ ከእጄ ሊያድናችሁ የሚችል አምላክ ማን ነው?”
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።