ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣ እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን?
እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’
ሁሉን ቻይ አምላክ ደስ ይለዋልን? ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን?
ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
በማያውቁህ ሕዝቦች ላይ፣ ስምህን በማይጠሩ፣ መንግሥታት ላይ፣ መዓትህን አፍስስ፤
“ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
ድኾችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።
ስለዚህ ይህን ሕዝብ በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እያደረግሁ፣ ዳግመኛ አስገርመዋለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።”
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
ስለዚህ ሕዝቤ ዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤ መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤ አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።
ያዕቆብን አሟጥጠው ስለ በሉት፣ ፈጽመው ስለ ዋጡት፣ መኖሪያውንም ወና ስላደረጉ፣ በማያውቁህ ሕዝቦች፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ፣ ቍጣህን አፍስስ።
ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ ገዦቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።
እናንተ ችግረኞችን የምትረግጡ፣ የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤
ከዚህም በላይ በሐሳባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ አይጠቅምም በማለታቸው፣ መደረግ የማይገባውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።
ነገር ግን እርስ በርሳችሁ የምትነካከሱና የምትበላሉ ከሆነ፣ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።