ከምሴሮት ተነሥተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።
የኤጽር ወንዶች ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን።
በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
ከሐሽሞና ተነሥተው በምሴሮት ሰፈሩ።
ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።
እስራኤላውያን ከብኤሮት ብኔያዕቃን፣ (ከያዕቃን ልጆች የውሃ ጕድጓዶች) ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛር በርሱ ምትክ ካህን ሆነ።