ከሐሽሞና ተነሥተው በምሴሮት ሰፈሩ።
ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም እዚያው ተራራው ጫፍ ላይ ሞተ። ከዚያም ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወረዱ፤
ከሚትቃ ተነሥተው በሐሽሞና ሰፈሩ።
ከምሴሮት ተነሥተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።
ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፣ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ።