ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።
የኤጽር ወንዶች ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን።
የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ እና አራን።
ከምሴሮት ተነሥተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።
ከሖርሃጊድጋድም ተነሥተው በዮጥባታ ሰፈሩ።
እስራኤላውያን ከብኤሮት ብኔያዕቃን፣ (ከያዕቃን ልጆች የውሃ ጕድጓዶች) ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛር በርሱ ምትክ ካህን ሆነ።
ከዚያም ተነሥተው ጉድጎዳ ወደ ተባለ ስፍራ፣ ቀጥሎም የውሃ ፈሳሾች ወዳሉባት ዮጥባታ ወደምትባል ምድር ተጓዙ።