ከእነርሱም ቀጥሎ የዕድሳቱ ሥራ የተከናወነው በኤፍራጥስ ማዶ በሚገኘው አገረ ገዥ ሥልጣን ሥር ባሉት በገባዖንና በምጽጳ ሰዎች በገባዖናዊው በመልጥያና በሜሮኖታዊው በያዶን ነበር።
ንጉሡ ገባዖናውያንን ጠርቶ አነጋገራቸው። ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ ከእስራኤል ወገን አልነበሩም፤ እስራኤላውያን ሊጠብቋቸው ቢምሉላቸውም፣ ሳኦል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ካለው ቅናት የተነሣ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነበር፤
እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ። ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።
ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ በራማ ሲሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት ወሰዱ፤ አሳም ጌባዕንና ምጽጳን ሠራበት።
የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ ለንጉሥ አርጤክስስ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤
ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ።