አሮጌውን በር የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም መልሰው ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ ማያያዣዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።
ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።
ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ በጎች በር ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም በዘበኞች በር አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።
የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሔ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንታቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም።