ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ የሆነው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል የሚቀጥለውን ክፍል ሠራ፤ ከሽቱ ቀማሚዎች አንዱ የሆነው ሐናንያ ደግሞ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። እነርሱም ሰፊው ቅጥር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ኢየሩሳሌምን መልሰው ሠሩ።
ከዚያም ዮሴፍ የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለመድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለመድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን በመድኀኒት ቀቡት።
ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለተኛው ቡድን በስተግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋራ ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤
እነዚህን በቀማሚ እንደ ተሠራ እንደሚሸት ቅመም የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት አድርግ፤ የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት ይሆናል።
የሞቱ ዝንቦች ሽቱን እንደሚያገሙ፣ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀልላል።
ሰዎች ወርቅ ከከረጢታቸው ይዘረግፋሉ፤ ብርንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ አንጥረኛን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ያበጅላቸዋል። እነርሱም ይሰግዱለታል፤ ያመልኩታልም።