እንዲሁም ብርቱ የሆኑት ወንድሞቹ 128 ሰዎች፤ የእነርሱም ዋና አለቃ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር።
እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር።
የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
ወንድሞቹ የሆኑት የየቤተ ሰቡ አለቆች 242 ወንዶች፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፤
ከሌዋውያኑ፦ የቡኒ ልጅ፣ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤
በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሸብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።
መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ዮሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ።