ከሌዋውያኑ፦ የቡኒ ልጅ፣ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤
ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣
የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
እንዲሁም ብርቱ የሆኑት ወንድሞቹ 128 ሰዎች፤ የእነርሱም ዋና አለቃ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር።
እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት የውጩ ሥራ ኀላፊዎች የነበሩት፣ ከሌዋውያን አለቆች ሁለቱ ሳባታይና ዮዛባት።