ወንድሞቹ የሆኑት የየቤተ ሰቡ አለቆች 242 ወንዶች፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፤
ቆሬያውያኑ ሕልቃና፣ ይሺያ፣ ዓዘርኤል፣ ዮዛር፣ ያሾብዓም፤
የቤተ መቅደሱን ሥራ ያከናወኑት ወንድሞቻቸው፣ 822 ሰዎች፤ የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤
እንዲሁም ብርቱ የሆኑት ወንድሞቹ 128 ሰዎች፤ የእነርሱም ዋና አለቃ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር።