ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን።
“አሁንም ጌታዬ በሰጠው ተስፋ መሠረት ስንዴውንና ገብሱን፣ የወይራ ዘይቱንና የወይን ጠጁን ለአገልጋዮቹ ይላክ፤
እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።
የሆነውንም ነገር ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ኢዮጴ ላካቸው።
በኢዮጴ ጣቢታ የተባለች አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጓሜ ዶርቃ ማለት ነው። እርሷም ዘወትር በትጋት በጎ ነገር እያደረገችና ድኾችን እየረዳች ትኖር ነበር።
ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች፣ ደቀ መዛሙርትም ጴጥሮስ በልዳ መሆኑን በሰሙ ጊዜ ሁለት ሰዎች ልከው፣ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና!” ሲሉ ለመኑት።
ይህም ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።
ጴጥሮስም ስምዖን ከተባለ ከአንድ ቍርበት ፋቂ ጋራ በኢዮጴ ብዙ ቀን ተቀመጠ።
ይሁድ፣ ብኔብረቅ፣ ጋትሪሞን፣
ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።