ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።
እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ።
ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦ “ዳን ከባሳን ዘልሎ የሚወጣ፣ የአንበሳ ደቦል ነው።”
ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን።
እነዚህ ለዳን ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።