በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤ በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል።
እነሆ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር።
ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ።
በውሃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይሸፍኑታል።
በሸንበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣ በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኰርማ መንጋ ገሥጽ፤ ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ ጦርነትን የሚወድዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።
ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤ የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል። ቀበሮዎች በተኙባቸው ጕድጓዶች፣ ሣር፣ ሸንበቆና ደንገል ይበቅልበታል።