በውሃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይሸፍኑታል።
በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤ በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል።
ወንዙ በኀይል ቢጐርፍም፣ አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስ እስከ አፉ ቢሞላም፣ እርሱ ተረጋግቶ ይቀመጣል።
ስለዚህ ያገኙትን ሀብት፣ ያከማቹትን ንብረት ከአኻያ ወንዝ ማዶ ተሸክመው ያሻግሩታል።
እነርሱም በለመለመ መስክ ላይ እንደ ሣር፣ በወንዝ ዳር እንደ አኻያ ዛፍ ይበቅላሉ።
“ ‘ከዚህ በኋላ ከምድሪቱ ዘር ወስዶ በመልካም ዐፈር አኖረው፤ ውሃ እንደ ልብ ባለበት ቦታ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ ተከለው፤
በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ፣ የለመለመ ዛፍ ቅርንጫፍ የአኻያ ዛፍ ቅርንጫፍ ይዛችሁ ሰባት ቀን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።