ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ።
ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”
“አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤
በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤ በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል።
ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤
መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።