እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው።
በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤ እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች።
“አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤
ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣ እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
ያለ ፍርሀት የተፈጠረ፣ እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።
ሰው በንስሓ የማይመለስ ከሆነ ግን፣ ሰይፉን ይስላል፤ ቀስቱን ይገትራል።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።