ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣ እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
ጅራቱ እንደ ጥድ ዛፍ ይወዛወዛል፤ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው።
እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው።
በላዬ ጠባቂ ታደርግ ዘንድ፣ እኔ ባሕር ነኝን ወይስ የባሕር አውሬ?
የቱን ያህል እልኸኛ እንደ ነበርህ ዐውቃለሁና፤ የዐንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም ናስ ነበር።