ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤ ዐውሎ ነፋስም በሌሊት ይዞት ይሄዳል።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።
የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤ በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።
ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ ተከትሎም ያሳድደዋል።
ሆዱን በሞላ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚነድድ ቍጣውን ይሰድበታል፤ መዓቱንም ያወርድበታል።
እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።
በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።
“ይሁን እንጂ፣ በውሃ ላይ የሚኵረፈረፍ ዐረፋ ናቸው፤ የወይን ቦታው ሰው የማይደርስበት፣ ርስታቸው ርጉም ነው።
እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።
የሞት ገመድ ዐነቀኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ።
በፏፏቴህ ማስገምገም፣ አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቀኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ ፊታቸውን በዕፍረት ሙላው።
እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤ እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤
እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኵር ልጅ ጀምሮ፣ በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እስካለው እስረኛ የበኵር ልጅ ድረስ ያለውንና የእንስሳቱን በኵሮች ሁሉ ቀሠፋቸው።
በዚያ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ፤
ጥልቅ ወደ ሆነው፣ ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ በላዬ ዐለፉ።