ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም።
በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዢነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል። ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።
ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?
የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣ የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣ በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?
ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሆኖም ይጠፋሉ፤ ዝቅ ዝቅ ብለው፤ እንደ ሌሎቹ ይከማቻሉ። እንደ እህል ራስም ይታጨዳሉ።
ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።
መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም? ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሷል፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”
አሁን የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ አያየኝም፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።
ጠላቶችህ ኀፍረት ይለብሳሉ፤ የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”
የእሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሰማው፣ ርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።
ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ።
በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፣ ወዲያው ይጠፋል፤ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበርራል።
በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደ ተጣለ ጕድፍ በምድር ላይ ይበተናል።
“ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ፤ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤
መንሹ በእጁ ነው፤ ዐውድማውን ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውን በጐተራ ይከትታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”