የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እርሱም አይገኝም፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል።
ከብርሃን ወደ ጨለማ ይጣላል፤ ከዓለምም ይወገዳል።
እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።
በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?
ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ።
ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፤ ስፍራውም ከእንግዲህ አያውቀውም።
ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።
እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
የእሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሰማው፣ ርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።
እንዲሁ በሞገድህ አሳድዳቸው፤ በማዕበልህም አስደንግጣቸው።
ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤ በመጥፊያቸው ቀን፣ ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”
በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።
ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።”