የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።
የአፋይም ወንድ ልጅ፤ ይሽዒ፣ ይሽዒም ሶሳን ወለደ። ሶሳን አሕላይን ወለደ።
የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ ፌሌት፣ ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።